ስለ ብሎገር ቴምፕሌት ትንሽ እናውራ፡፡ በአጭሩ ቴምፕሌት የዌብ ዲዛይን አካል ነው፡፡ ብሎገር ቴምፕሌት ደግሞ ለብሎገር ተጠቃሚዎች ተብሎ የሚሰራ ቴምፕሌት ነው፡፡ የራሱ የሆነ የአሰራር መንገድም አለው፡፡ የብሎገር ቴምፕሌት ሰሪ ይበልጥ ስለ ቅልጥፍና እና ስለ ውበት ይጨነቃል፡፡ ውብ ቴምፕሌት መስራት አርት ነው፡፡ ደስ ይላል፡፡ ግን እጅግ አድካሚ ስራ ነው፡፡ የወገብም የአይንም ጠር ነው፡፡ እንደ የትኛውም አርት ስራ ሰሪው በውጤቱ ስለሚያገኘው ሳቲስፋክሽን ብሎ ነው የሚገባበት፡፡ ከቢዝነስ አንግልም ቆንጆ ነው፡፡ በኛ ሃገር ሁኔታ ግን እጅግ እጅግ ቢከብድም፡፡
አንዳንድ ሃገር በጣም ከመለመዱ የተነሳ የወሩ ምርጥ ቴምፕሌት ዲዛይን የሚል ውድድር ሁሉ አላቸው፡፡ ሃሳቡ ስላላቸው ቢያንስ በራሳቸው ሰርክል ማስታወቂያ የመሰራራት እድሉም ሰፊ ነው፡፡ እዚህ ለብዙ ሰው ሃሳቡ አዲስ ነው፡፡ በተመሳሳይ ሙያ ወስጥ ላሉም ጭምር፡፡ እስከዛሬ በግል አንድ ሰው ብቻ ነው ሃሳቡ ያለው የገጠመኝ፡፡ ይሄን ማሰብ ምን ያህል ሰቅጣጭ እንደሆነ አስቡት፡፡ ስለዚህ ከቢዝነስ አንግል መስመሩ ያለው ውጪ ብቻ ነው፡፡ ኦንላይን ማለትም ይቻላል፡፡ በሰው በሰው መሸጥ መቶ በመቶ መስመሩ ዝግ ነው፡፡ ያንተ አይነት ዌብሳይት ስራልኝ የሚልን ድንገት ከሰማይ የወረደን ሰው ከቢዝነስ አንግል ማሰብ ፌዝ ስለሆነ፡፡
ስለዚህ ስራው ውጪ መሆኑ ውድድሩን እጅግ ከባድ ያደርገዋል፡፡ ብዙ ተግዳሮትም አለው፡፡ ከክፍያ ሲስተም እስከ ሌብነቱ ማለት ነው፡፡ በራስ መንገድ ለመሸጥ የራስ ሰው ያስፈልጋል፡፡ ይሄ ደሞ ሃገር ውስጥ ዝግ ነው፡፡ በሰው መንገድ ለመሸጥ ደግሞ በሰው ፍላጎት መሄድን ይፈልጋል፡፡ እኔ ምን ያስደስተኛል ሳይሆን ሻጩ ምን ይፈልጋል የሚል፡፡ ይሄን እንኳ ተቋቁሞ ቢታለፍ ሌብነቱ ከባድ ነው፡፡
ለምሳሌ አንድ ሰው ወራት ተጨንቆ ጎብጦ ለፍቶ የሰራው ቴምፕሌት የአንዱ መሸጫ ዋጋ 10 ዶላር ነው እንበል፡፡ አንድ ሌባ በ10 ዶላር ይገዛና በራሱ መሸጫ በ5 ዶላርም በ1 ዶላርም ይቸበችበዋል፡፡ ምናገባው አለፋበት፡፡ ብዙ ሌባ ሳይቶች እጠቁማችሁ ነበር ግን አስፈላጊ አይደለም፡፡ ኢንዶኔዢያ፣ ህንድ መሰል ሃገራት ውስጥ እጅግ የተለመደ ስራ ነው፡፡ የቴምፕሌት ኦሪጂናል ሰሪው ምንድነው ትርፉ ስም ብቻ፡፡ ምክንያቱም ቴምፕሌት ዴሞ ላይ የሚታየው የሱ ስም ነው፡፡ ቀፋፊው ክፍል ግን በሌባ ቴምፕሌት መሸጫ ላይ ቴምፕሌቱ ቤስት ሴለር ተብሎ ሰሪው ሰባራ ሳንቲም አለማግኘቱ ነው፡፡ ይሄን በሆነ አጋጣሚ ያየ ሰው ዴሞው በቴምፕሌት ሰሪው ስም ስለሆነ፣ ቴምፕሌት ሰሪውን ባለብዙ ገንዘብ አርጎ ሊያስበው ይችላል፡፡ እና ይሄን ሁሉ እያወቀ ቴምፕሌት ሰሪው ለምን ይለፋል? ስለ ፍቅር ሲል ይመስለኛል፡፡ ተመሳሳይ የአርት ስራ አዙሪት ነው ነገሩ፡፡
እድሉ ኖሮት ቴምፕሌት ሰሪ የራሱን ቴምፕሌት ራሱ የሚሸጥ ከሆነ ግን ለዚህ መፍትሄው ለያንዳንዱ ቴምፕሌት የራሱን license key ማዘጋጀት ነው፡፡ እንደዛም ሆኖ ዘራፊዎች ከነ ላይሰንስ ኪዩ ይቸበችቡታል፡፡ ከ11 አመት ቆይታ በኋላ ከስራው ጋር ልለያይ አካባቢ አንድ መፍትሄ አግኝቼ ነበር፡፡ ከአንድ ሰው ውጪ በፍፁም የማይሰራ ላይሰንስ ኪይ ማዘጋጀት፡፡
ምናልባት እኔ ከዚ ስራ ስለወጣሁ እኔ ጋር ከሚቀር የሆነን ሰው የሚጠቅመው ከሆነ እዚህ ላጋራው ብዬ ነው፡፡ እኔ ጋር ተቀምጦ ከሚሞት ፍሬ ካፈራ የሆነ ቦታ ይቀመጥ፡፡ በዚህ አጋጣሚ በ11 አመታት የተሰበሰቡ ከ300 በላይ ፕሪምየም ቴምፕሌቶች ስላሉኝ በአንድ ዌብሳይት ላይ እያስገባዋቸው ስለሆነ ስጨርሰው ሊንክ አረገዋለሁ፡፡ እያንዳንዳቸው ከ5 ዶላር እስከ 28 ዶላር የወጣባቸው ናቸው:: እጅግ አሰልቺ ስራ ስለሆነ ነው አሁን በአሁን የማላረገው፡፡ አንዱን ቴምፕሌት ዳታ ለማስገባት ፕሮሰሱ እጅግ እጅግ ብዙ ነው፡፡ ግን በጣም ኢንተረስትድ የሆነ ሰው ካገኘሁ ፍላጎቱን እያየሁ በውስጥም ልልክለት እችላለሁ፡፡
ወደ ላይሰንስ ኪዩ እንሂድ…
እንደሚታወቀው ብሎገር ለአንድ ተጠቃሚ አንድ ዩኒክ Blogld አለው፡፡ ቴምፕሌት የሚሰራ ሰው ብሎግ አይዲ እንዴት እንደሚታወቅ አይጠፋውም ብዬ ነው አፈላለጉን የዘለልኩት፡፡ እንቀጥል....
ሁሉም ብሎግ አይዲ ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ 1178960850240742892 የአንድ ብሎገር ተጠቃሚ ብሎግ አይዲ ነው፡፡ ሃሳቡ የመጣው ይሄንን ብሎግ አይዲ ማዕከል ያረገ ላይሰንስ ኪይ መፍጠር ነው፡፡ ከአንድ ብሎገር ቴምፕሌት ሰሪ ጋር እንደ ሃሳብ አውርተንበት እኔ መሬት ያወረድኩት ስራ ነው፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ ይሄን ብሎግ አይዲ ሰው እንዳያውቀው ኢንክሪፕት እናደርገዋለን። የራሳችን ሚስጥር ነው ይሄ... ይሄንን በምን መንገድ ኢንክሪፕት እንዳደረግነው ማንም ሰው ማወቅ የለበትም፡፡
ይሄን ማድረጊያ ፈንክሽናችን ይሄ ነው፡፡ ይሄ የግል የሚስጥር ፈንክሽናችን ነው፡፡
function encryptLicenseValue(value) {
let encryptedValue = '';
for (let i = 0; i < value.length; i++) {
encryptedValue += String.fromCharCode(value.charCodeAt(i) + 22);
}
return encryptedValue;
}
console.log(encryptLicenseValue("1178960850240742892"));
ከላይ እንደምታዩት መጨረሻ የምናስገባው ቁጥር የብሎገሩን ብሎግ አይዲ ነው፡፡ በውጤቱም ቁጥሩን ወደ ፊደል ይቀይርልናል፡፡ ልክ እንደዚ GGMNOLFNKFHJFMJHNOH፡፡ የዛ ብሎገር ላይሰንስ ኪዩ ይህ የተቀየረው ፊደል ነው:: ይሄንን ሌላ ቦታ ለብቻችን የምንሰራው ስራ ነው፡፡ ስያሜውን natidanlicense ነው ያልኩት፡፡ ናቲዳን ላይሰንስ ነው፡፡
በነገራችን ላይ አንዳንድ ቴምፕሌት ሻጮች የሚያዘጋጁት ላይሰንስ ኪይ አለ፡፡ ግን ዩኒክ ስላልሆነ ከነ ላይሰንስ ኪዩ ሌላም ሰው መጠቀም ይችላል፡፡ የገዛው ሰው መልሶ ለሌላ ሰው መሸጥ ይችላል፡፡ እኔ እያሳየዋችሁ ያለሁት ግን ይሄን ችግር ከነ አካቴው የሚቀርፍ ነው:: ከአንድ ሰው ውጪ በምንም መንገድ አይሰራም፡፡
ቀጥለን ወደ ብሎጋችን እንሄዳለን።
Head ውስጥ ባለ script ውስጥ ቀጣዩን እናስገባለን፡፡ ከዛ አጠቃላይ ስክሪፕቱን ለሌባ እንዳይመች obfuscate አድርጎ መደበላለቅ ነው፡፡ ቴምፕሌት ስራ ውስጥ ያለ ሰው obfuscate አደራረጉን በደንብ ይረዳዋል፡፡ ይሄን ሁሉ የምናረግበት አላማ እኛ ካዘጋጀነው ብሎግአይዲ ውጪ የሆነ ማንኛውም ብሎገር ቴምፕሌቱን እንዳይጠቀም ማድረግ ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ውጤቱ የሚሆነው:- ከናቲዳን ላይሰንስ ውጪ የሚጠቀም ብሎገር ካለ ዌብሳይቱን ወደ ሌላ ዌብሳይት ሳይፈልግ ይቀየርበታል፡፡ ለምሳሌ ተጠቃሚው ሰርቆ ከሆነ የሚጠቀመው ዌብሳይቱን አየር ላይ እንዲቀይርበት የኔን ዌብሳይት https://eriyotalemu.com/ አስገባለሁ።
እናንተ ወደምትፈልጉት ታደርጉታላችሁ።
window.onload = function(){
if(document.getElementById("natidanlicense") == null){
// Do something here if the ID is NOT found on the page
window.location.href = "https://eriyotalemu.com/";
}
Style ውስጥ ከቀጣዩ መስመር በፊት
]]></b:skin> ይሄን ታስገባላቹ።
#natidanlicense{display:none;}
አላማው ላይሰንሱ አደባባይ እንዳይሰጣ ማድረግ ነው።
Layout ላይ ከheader በታች ነው የሚሆነው ላይሰንስ ኪይ ማስገቢያ ሴክሽን ትፈጥራላቹ። ቀጣዮን ይመስላል።
<b:section class='license' id='widget-license' name=' ' showaddelement='false'>
<b:widget id='HTML225' locked='true' title='License' type='HTML' version='2' visible='true'>
<b:widget-settings>
<b:widget-setting name='content'>GGMNOLFNKFHJFMJHNOH</b:widget-setting>
</b:widget-settings>
<b:includable id='main'>
<div id='natidanlicense'><data:content/></div>
</b:includable>
</b:widget>
</b:section>
ከላይ የምታዩት GGMNOLFNKFHJFMJHNOH የተጠቃሚው ላይሰንስ ነው። ላይሰንስ አስገባ የሚለው ቦታ ላይ የሚያስገባው ይሄንን ነው።
በመጨረሻም </body> በላይ ቀጣዩን ፈንክሽን እናስገባለን። ቀደም ብለን በሚስጥር ኢንክሪብት ያረግነውን ላይሰንስ ዲክሪፕት አድርጎ ከብሎግ አይዲው ጋር የሚያመሳክርልን ፈንክሽን ነው። ልክ ከሆነ ያልፈዋል። ልክ ካልሆነ ዌብሳይቱን ወደ ባለቤቱ ይመልሰዋል።
function decryptLicenseValue(encryptedValue) {
let decryptedValue = '';
for (let i = 0; i < encryptedValue.length; i++) {
decryptedValue += String.fromCharCode(encryptedValue.charCodeAt(i) - 22);
}
return decryptedValue;
}
const natilicenseDiv = document.getElementById('natidanlicense');
const encryptedLiyulicense = natilicenseDiv.innerText.trim();
const decryptedLiyulicense = decryptLicenseValue(encryptedLiyulicense);
var blogIdMeta = document.querySelector('meta[itemprop="blogId"][content]');
if (blogIdMeta) {
var blogIdValue = blogIdMeta.getAttribute('content');
if (decryptedLiyulicense === blogIdValue) {
validLicense = true;
} else {
validLicense = false;
window.location.href = "https://eriyotalemu.com/";
}
}
ከዛ ከላይ እንዳደረግነው obfuscate ማድረግ ነው። በምንም መልኩ ማንም ሰው ሊዘርፋችሁ አይችልም።የኦንላይን ሌባ እሳት የላሰ ቢሆን እንኳ ይሄን በፍፁም መዝረፍ አይችልም።
አሁን ይሄን እዚህ የፃፍኩትን በእንግሊዘኛ ፅፌው ቢሆን ኖሮ ስለ ብሎገር የሚፅፉ ዌብሳይቶች አየር ላይ ነበር የሚዘርፉኝ። ይሄ የትም የማታገኙት ኦሪጅናል ፅሁፍ ነው። ወደፊት ተርጉሞ የሚዘርፈኝ ከመጣ ይመቸው ከማለት ውጪ ምንም አልልም። ያው ከኔ ይውጣ ነው ሃሳቡ። እኔ ጋር ተቀምጦ ምንም አይጠቅመኝም። አሁን የብሎገር ቴምፕሌት ለሚሰራ ግን ራስ ምታቱን ያቀልለታል።
ከአምስት ስድስት አመት በፊት እዚህ ሃሳብ ላይ የደረስኩት ለኔ እጅግ መልካም ነበር። እኔ ጫማ ስሰቅል መፍትሄ ማግኘቴ ለኔ ሳይሆን ጥቅሙ ለሌላ ሰው ነው ማለት ነው። ያው ህይወት እንደዚህ ነው መፍትሄ ሁሉ ለራስ ጥቅም ብቻ አይዘጋጅም። የአንዱ ላንዱ እየሆነ ነው እዚህ የደረስነው። ይሄም ይቀጥላል።